የአጠቃቀም መመሪያ
1. መግቢያ
ወደ ኢትዮጵያ ዲጂታል ሎተሪ አገልግሎት ድህረገፅ እንኳን ደህና መጡ። በዚህ ድህረገጽ ላይ የሚገኙት ጨዋታዎች፣ማለትም፦ ቶምቦላ፣ ራፍል፣ ባህላዊ ሎተሪ፣ ፈጣን ሎተሪ፣ ፋቅ ፋቅ፣ የዘፈቀደ ቁጥር መምረጥ፣ ቢንጎ፣ ሎቶ ጃክፖት ፣ መስበር (ክራሽ)፣ ምናባዊ (ቨርቹዋል) ጨዋታዎች፣ እና ተመሳሳይ ሌሎች የዕጣ አይነቶች ናቸው። በእነዚህ ጨዋታዎች ላይ ከመሳተፍዎ በፊት፣ በሚከተሉት ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ እና ሁኔታዎች በሙሉ ለመገዛት የሕግ ግዴታ እንደገቡ ተስማምተዋል፡፡ እባክዎ ከመግባትዎ በፊት እነዚህን ደንብ፣ መመሪያና ሁኔታዎች በትኩረት ያንብቡ።
የዲጂታል ሎተሪ መለያ በመፍጠር እና በማንኛውም ጨዋታ ውስጥ በመሳተፍ፣ እነዚህን ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ እና ሁኔታዎች በሙሉ እንደሚያከብሩ በግልጽ ተስማምተዋል።
2. ብቁነት
- በዚህ አገልግሎት ላይ የሚሳተፉ ሁሉ ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላባቸው መሆን አለባቸው።
- ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕጎችን እንደሚያከብሩ ለማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
- የዲጂታል ሎተሪ አቅራቢው ድርጅት፣ የሶፍትዌር አበልፃጊ ሠራተኞች፣ እና የቅርብ ቤተሰብ አባላት (ለምሳሌ፦ ባል/ሚስት፣ ልጆች፣ ወላጆች) በዚህ ጨዋታ ላይ መሳተፍ አይችሉም።
3. የአካውንት ምዝገባ
- ተጠቃሚዎች በመለያ ምዝገባ ጊዜ ትክክለኛ እና ሙሉ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጠቃሚዎች የመለያ ማረጋገጫ መረጃዎቻቸውን (የይለፍ ቃል እና ተጠቃሚ መለያ) ሚስጥራዊነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው።
የምዝገባ መስፈርቶችሀ) ሙሉ የሕጋዊ ስም (ግዴታ)
ለ) የሚሰራ ማንነትን የሚያሳይ መታወቂያ (አማራጭ)
ሐ) የሚሰራ የሞባይል ስልክ ቁጥር (ግዴታ)
መ) የሞባይል ገንዘብ አካውንት (ግዴታ ገንዘብ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ወጪ ለማድረግ)
ሠ) የኢትዮጵያ ባንክ ሒሳብ ማስረጃ (ግዴታ ያሸነፉትን ገንዘብ ለመቀበል)
ረ) የሚሰራ ኢሜይል አድራሻ (አማራጭ)
ሰ) የመኖሪያ አድራሻ (አማራጭ)
የመለያ ደህንነት ለመጠበቅሀ) ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም
ለ) ድርብ-ደረጃ ማረጋገጫ ስርዓት መጠቀም
ሐ) የደህንነት መደበኛ ማዘመኛ ማድረግ
መ) ፈጣን የደህንነት ችግር ሪፖርት ማድረጊያ መጠቀም
4. የተሳትፎ ህጎች
- እያንዳንዱ የሎተሪ ትኬት ወይም የጨዋታ ግዢ አንድ ዕጣ ላይ ለመግባት ወይም ለአንድ ፈጣን ድል ብቻ የሚያገለግል ነው።
- ትኬቶች ትክክለኛ የክፍያ ዘዴዎች በመጠቀም መገዛት አለባቸው።
- ለእያንዳንዱ ጨዋታ የሚከፈለው ክፍያ በጨዋታው ላይ የተወሰነ ሲሆን፣ በልዩ ሁኔታ ካልተገለጸ በስተቀር የተገዛ ትኬት ማስመለስም ሆነ ማሰረዝ አይቻልም።
- ሁሉም ተሳትፎዎች በድርጅታችን በኩል በተረጋገጡና እውቅና በተሰጣቸው መድረኮቻችን፤ በድህረ-ገጽ፣ በመተግበሪያችን ወይም በተፈቀደላቸው ግለሰቦች/ተቋማት በኩል ብቻ መከናወን አለባቸው።
- ከፈጣን ድል ወይም ከዕጣ መውጣቱ ቀን በፊት ሙሉ ክፍያ የተደረገባቸው የትኬት ግዢ፣ የጨዋታ ግዢና የዕጣ ተሳትፎዎች ብቻ ተቀባይነት አላቸው።
- የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በአንድ ተጠቃሚ የሚገዙትን ትኬቶች ብዛት የመገደብ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የዕጣ ውስጥ ተሳትፎሀ) የግዢ የመጨረሻ ቀን፦ በልዩ ሁኔታ ካልተገለጸ በስተቀር ዕጣ ከመውጣቱ ከ1 ሰዓት በፊት ይጠናቀቃል፡፡
ለ) ከዕጣ መውጣቱ በፊት የዲጂታል ትኬት ማረጋገጫ መድረስ አለበት።
ሐ) የተለያዩ የተሳትፎ አማራጮች ይቀርባሉ።
መ) የክፍያ ማረጋገጫ መኖር አለበት።
የፈጣን የዘፈቀደ ቁጥር ጨዋታዎች መግባትሀ) ተጫዋቾች ወዲያውኑ ጨዋታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
ለ) በዲጂታል መንገድ ፋቅ ፋቅ ጨዋታዎችን ማድረግ ይቻላል፡፡
ሐ) የጨዋታውን ውጤት ወዲያውኑ ማየት ይቻላል፡፡
መ) የሽልማት ማሳወቂያ አለው፡፡
5. የዕጣ ሂደት
- ዕጣዎች በተረጋገጠ ቴክኖሎጂ ወይም በሰው ኃይል የሚዘጋጅ የሎተሪ ዕጣ ማውጫ መሳሪያ በመጠቀም ይፈጸማል።
- ዕጣዎች በተወሰነ ጊዜ የሚካሄዱ ሲሆን ውጤቱም በድረ-ገጽ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ወይም ቀጥታ ስርጭቶች በኩል ይፋ ይሆናል። በይፋ የተገለጹት ውጤቶች የመጨረሻ ናቸው።
ለፈጣን ጨዋታዎች የዕጣ ሒደት: ሀ) ሽልማቶች በቅድሚያ የተወሰኑ ናቸው።
ለ) ደህንነቱ የተጠበቀ የአወጣጥ ስርዓት ይከተላል።
ሐ) ወዲያውኑ የማረጋገጥ አሰራር አለው፡፡
መ) ራስ-ሰር የሽልማት ምደባ አለው፡፡
- በቴክኒክም ሆነ በዕጣ ማውጫ ስርዓት ምክንያት ችግር ሲያጋጥም የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዕጣውን ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በዕጣ አወጣጡ ላይ አለመግባባት ቢከሰት፣ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል።
6. የሽልማት ህጎች
- ለእያንዳንዱ የሎተሪ ጨዋታ ወይም ዕጣ የሚሰጠው ሽልማት በይፋዊ መድረኮቻችን በኩል እንደተገለጸው ይሆናል።
- አሸናፊዎች በኢሜይል፣ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) እና በፕላትፎርማችን በኩል ይታወቃሉ፤ አሸናፊዎችም ሽልማታቸውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መጠየቅ አለባቸው።
- በጊዜ ገደቡ ያልተጠየቁ ሽልማቶች ሊሰረዙ ወይም ወደ ሌላ ዓላማ ሊሸጋገሩ ይችላሉ።
- ሁሉም ሽልማቶች በተገለጹበት መልኩ የሚሰጡ ሲሆን በይፋ ካልተገለጸ በስተቀር በጥሬ ገንዘብ ወይም በሌላ ጥቅማጥቅሞች ሊቀየሩ አይችሉም።
7. ማረጋገጫ
- አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ከመጠየቃቸው በፊት ትክክለኛ መታወቂያ እና በሎተሪ ጨዋታው ላይ ለመሳተፍ ብቁ መሆናቸውን የሚያመለክት ህጋዊ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠየቃሉ።
- በዚህ ጊዜ ማንኛውም የሐሰት ወይም የተሳሳተ መረጃ ለመስጠት የሚደረግ ሙከራ የሽልማት ጥያቄውን ውድቅ ያደርጋል፤ እንዲሁም ህጋዊ ተጠያቂነት ያስከትላል።
8. ተጠያቂነት
- የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እና ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን የድረ-ገጽ ደህንነት ጥበቃ፣ ፍትሐዊ ጨዋታ፣ የሽልማት ክፍያ እና የተጠቃሚዎችን መረጃ ጥበቃ በሚመለከት ኃላፊነት ይወስዳሉ።
- የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በተጠቃሚ ስህተት ምክንያት ለጠፉ፣ ለዘገዩ እና ለተሳሳቱ ተሳትፎዎች፣ የባንክ ክፍያ መዘግየት ወይም በቴክኒካዊ ችግር ምክንያት ለተሳሳቱ መረጃዎች ተጠያቂ አይሆንም።
- በድረ-ገጹ ላይ በተፈጠረ ስህተት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር፣ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በሎተሪ ዕጣና ጨዋታዎች ምክንያት ለሚከሰቱ ኪሳራዎች፣ ጉዳቶች፣ ጥፋቶች እና በሽልማት ገንዘብ አጠቃቀም ለሚመጡ ጉዳዮች ተጠያቂ አይሆንም።
- የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከአቅም በላይ የሆኑ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት ዕጣውን የመቀየር፣ የመሰረዝ ወይም የማገድ መብቱ የተጠበቀ ነው
9. ያልተሳካ ክፍያ እና የትኬት እርግጠኝነት (Failed Payments & Ticket Validity)
1. ክፍያዉ ያልተጠናቀቀ (Incomplete Transactions)ክፍያ ከባንክ/በክፍያ መተግበርያ ስርዓት ያልተሳካ ከሆነ፣ የተመረጠው የሎተሪ ቁጥር ውድቅ ይሆናል።
ስርዓቱ “ክፍያ ተጠናቋል” ቢልም፣ በትክክል ገንዘብ ካልገባ፣ ትኬቱ ውድቅ ይሆናል።
2. የተበላሸ የክፍያ ሂደት (Payment Processing Errors)በቴክኒካል ችግር፣ የኢንተርኔት መቋረጥ፣ ወይም የስርዓት ስህተት የተፈጠረ ትኬት ትኬቱ ውድቅ ይሆናል።
3. እርግጠኝነት ያለው የትኬት ማረጋገጫ (Valid Ticket Confirmation)ቲኬት የሚቆጠርበት ብቸኛ መስፈርት፦ ሙሉ በሙሉ የተከፈለ እና በስርዓቱ የተረጋገጠ ክፍያ ሲሆን ብቻ ነው።
• የማጭበርበር መከላከያ አጣራ (Fraud Prevention Clause)ማንኛውም ሰው በማሳሳት የክፍያ ማረጋገጫ በመጠቀም ወይም ያልተከፈለ ትኬት በመጠቀም ሽልማት ለማግኘት ከተሞከረ፣ መለያው ይታገዳል እና የህግ እርምጃ ይወሰድበታል።
10. የግብር ጉዳዮች
- አሸናፊዎች ከሽልማታቸው ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ግብሮች ወይም ክፍያዎች የመክፈል ኃላፊነት አለባቸው።
- የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በሕጉ መሰረት የግብር ተቀናሾችን የገቢዎች ሚኒስቴርን ወክሎ ሊይዝ ይችላል።
11. የተከለከሉ ተግባራት
- ማንኛውም የማታለል፣ የመለያ ጥፋት፣ የክፍያ ማታለል፣ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
- ትኬቶችን ለመግዛት ወይም በሎተሪ ለመሳተፍ ራስ-ሰር ስርዓቶችን እና አስተማማኝ ያልሆኑ ስርዓቶችን (ቦቶች) መጠቀም የተከለከለ ነው።
- ከላይ የተዘረዘሩትን የተከለከሉ ድርጊቶች መፈጸም በድርጊቱ ዓይነት ወይም ደረጃ መለያ መታገድ፣ ሽልማት መወረስ፣ በቋሚነት አገልግሎቱን ከመጠቀም መታገድ እና ህጋዊ ተጠያቂነት የሚያስከትሉ እርምጃዎችን ያስወስዳል።
12. መቋረጥ
- የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እነዚህን ውሎች እና ሁኔታዎች የሚጥሱ ተጠቃሚዎችን መለያ ለማገድ ወይም አገልግሎቱን እንዳይጠቀሙ የማቋረጥ መብት አለው።
- የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በሚያደርጉት አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች፣ በቁጥጥር ደንቦች ወይም በድረ-ገጹ ስራ ማቆም ወይም መዘጋት ምክንያት መለያቸውን ለማገድ ወይም አገልግሎቱን እንዳያገኙ የማቋረጥ መብት አለው።
- የመድረኩን ፖሊሲ እንዳለ ሆኖ ተጠቃሚዎች፣ በፅሁፍ ጥያቄ በማቅረብ አካውንታቸውን በማንኛውም ጊዜ ማዘጋት ይችላሉ።
13. ማሻሻያዎች
- የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ውሎችን፣ ደንቦችን፣ ሽልማቶችን፣ ወይም የአሰራር ሥነ ሥርዓቶችን በማንኛውም ጊዜ ለመለወጥ፣ ለማሻሻል ወይም ለመቀየር የማይገደብ መብት አለው።
- ተጠቃሚዎች የተደረጉ ለውጦችን ወይም ማሻሻያዎችን በድህረገጹ፣ በስልክ የጽሑፍ መልክት በኢሜይል ማሳወቂያ ወይም በሌላ አማራጭ መረጃ ያገኛሉ፡፡
14. ተፈጻሚነት ያለው ሕግ
- እነዚህ ውሎች፣ ደንብና እና ሁኔታዎች በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ይመራሉ።
- ማንኛውም አለመግባባት ወይም ቅራኔ በብቸኛ የሕግ ቤቶች ውሳኔ በሚሰጠው መልኩ ይፈታል።
15. የደንበኛ ድጋፍ
- በዲጂታል ሎተሪ መድረኩ ለደንበኞች 24/7 ድጋፍ በተለያዩ አማራጭ መንገዶች ይሰጣል፡፡
- በብዙ መንገዶች (ቻት፣ ስልክ፣ ኢሜይል) እርዳታውን ማግኘት ይቻላል፡፡
- በ ሰዓታት ውስጥ ምላሽ ይሰጣል፣ ችግሩ ይፈታል፡፡
16. አለመግባባቶች የሚፈቱበት መንገድ
- በውስጥ ግምገማ ሊፈታ ይችላል፡፡
- በሶስተኛ ወገን አማካይነት በስምምነት ሊፈታ ይችላል፡፡
- በሕግ አግባብ እንዲፈታ ይደረጋል፡
17. ግላዊነት
- በሎተሪውና ጨዋታዎቹ ላይ ተሳትፎ በማድረግ፣ የግል መረጃዎትን በ“ግላዊነት ፖሊሲ” መሰረት እንደሚሰበሰብ፣ ጥቅም ላይ አንደሚውልና ሊከማች እንደሚችል አውቀው ፈቃድዎን እንደሰጡ ይቆጠራል፡፡
- የግል መረጃዎትን የምንጠቀመው ዕጣ ለማውጣት፣ ሽልማት ለመስጠትና ለማስታወቂያ ብቻ ሲሆን፣ ፈቃድዎትን እስካልሰጡ ወይም የሕግ ግዴታ ካልተጣለብን በቀር ለሌላ ማንም ሦስተኛ ወገን አናጋራም፡፡