መነሻ ገፅሎተሪ ይግዙፈጣን ጨዋታዎችን ይጫወቱውጤቶች

የግላዊነት ፖሊሲ

1. መግቢያ

1.1 ቁርጠኛነት መግለጫ

እንኳን ወደ ኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በደህና መጡ። የግል መረጃዎን ለመጠበቅ እና የባለቤትነት ግላዊሚስጥርዎን ለማክበር ቁርጠኞች ነን። ይህ የባለቤትነት ግላዊ ሚስጥር ጥበቃ (ፖሊሲ) የግል መረጃዎትን እንዴት እንደምንሰበስብ፣ እንደምንጠቀምበትና እንደምናስተዳድር እንዲሁም የጥበቃ ሥርዓታችንን በዝርዝር ያብራራል።

መለያ በመፍጠር ወይም አገልግሎታችንን በመጠቀም፣ በዚህ ፖሊሲ ውስጥ በተዘረዘሩት ደንቦች እንደተስማሙና እንደተቀበሉ ይቆጠራል።

1.2 የፖሊሲ ተፈጻሚነት

ይህ ፖሊሲ በሁሉም የዲጂታል ሎተሪ አገልግሎቶች፣ በዕጣ በሚወሰኑ ሎተሪዎች፣ በፈጣን ጨዋታዎች እንዲሁም ከእነዚህ ጋር ተያይዘው በድህረገጹና መተግበሪያዎች ላይ የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ተፈጻሚ ነው፡፡

2. የምንሰበስበው መረጃ

የሚከተሉትን የግል መረጃዎን ልንሰበስብ እና ልንጠቀምባቸው እንችላለን።

  • 2.1 የግል መለያ፡ ስም፣ የትውልድ ቀን፣ ጾታ እና መለያ ቁጥሮች።
  • 2.2 የመለያ መረጃ፦ የተጠቃሚ መለያ እና የይለፍ ቃል
  • 2.3 የመገኛ መረጃ፦ አድራሻ (ኢሜይል እና ስልክ ቁጥር)
  • 2.4 የግብይት መረጃ፦ የባንክ አካውንት እና የክፍያ ዝርዝሮች
  • 2.5 ቴክኒካዊ መረጃ፡- የአይ ፒ አድራሻ፣ ድረ-ገጽ የሚጠቀሙበት የብራውዘር አይነት እና በኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት የሚሰበሰቡ አጠቃቀምዎን የሚያሳዩ መረጃዎች ።
  • 2.6 የማረጋገጫ መረጃ፦ የመታወቂያ ሰነዶች ኮፒዎች ወይም የአገልግሎት ጥያቄዎች

3. መረጃዎን እንዴት እንደምንሰበስብ

የግል መረጃዎትን በሚከተሉት መንገዶች እንሰበስባለን፦

  • 3.1 ቀጥተኛ ግንኙነቶች፦ መለያ ለመፍጠር ሲመዘገቡ፣ ቲኬት ሲገዙ፣ ጨዋታ ላይ ሲሳተፉ፣ ሽልማት ሲጠይቁ ወይም ከእኛ ጋር መልዕክት ሲለዋወጡ፡፡
  • 3.2 በራስ-ሰር ቴክኖሎጂዎች፦ ድህረ ገጻችንን ወይም መተግበሪያዎቻችንን ሲጠቀሙ በአናሊቲክስ ወይም ለድህረገጽ ቁጥጥር በሚሰበሰብ ቴክኒካዊ መረጃ
  • 3.3 ከሦስተኛ ወገኖች፦ በክፍያ መሠብሠብ፣ በማንነት ማጣራትና ማረጋገጥ እንዲሁም በማርኬቲንግ ስራዎች ከሚረዱን አገልግሎት አቅራቢዎች።

4. የግል መረጃዎን የምንጠቀምበት ምክንያት

የግል መረጃዎን ለሚከተሉት አላማዎች እንጠቀማለን፡-

  • 4.1 የሎተሪ አገልግሎታችንን ወደእርስዎ ለማድረስና በአግባቡ ለማስተዳደር።
  • 4.2 የሚያከናውኗቸው ግብይትዎን በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም እና አካውንትዎን ለማስተዳደር።
  • 4.3 ማንነትዎን ለማጣራት እና ህጋዊ ግዴታዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ።
  • 4.4 ስለተሻሻሉ አገልግሎቶቻችን፣ ስለ ፕሮሞሽኖቻችን እና ስለደንበኞች አገልግሎት መረጃዎችን ወደእርስዎ ለማድረስ።
  • 4.5 በአጠቃቀም ወቅት የሚያጋጥምዎትን ችግሮች በመመርመር የአገልግሎቶቻችንን ጥራት ለማሻሻል እና የእርስዎን እርካታ በየጊዜው ከፍ እንዲል ለማስቻል።
  • 4.6 ደህንነትዎን ለማረጋገጥ እና ማጭበርበርን ለመከላከል፡፡

5. የአጠቃቀም ህጋዊ መሠረት

5.1. የግል መራጃዎትን በሕጋዊ፣ ፍትሃዊ፣ እና ግልጽነት ባለው መልኩ በሚከተሉት ላይ ተመስርቶ ይቀናብራል፦

  • ሀ) ፈቃድ፡- የግል መረጃዎን ለመጠቀም በግልጽ የእርስዎን በጎ ፍቃድ በማግኘት።
  • ለ) የውል ግዴታ፡- ከእርስዎ ጋር ያለንን ውል ለመፈጸም።
  • ሐ) ህጋዊ ግዴታ፡- ከምንሰራው ስራ ጋር ተያያዥ የሆኑ ህጎች እና መመሪያዎችን ለማክበርና ተፈጻሚ ለማድረግ።
  • መ) አግባብነት ያለው መብት፡- ስራችንን ለማስተዳደር እና አገልግሎቶቻችንን ለማሻሻል።

5.2. የግል መረጃዎት የሚቀናበረው የሚከተሉትን ሕጋዊ ግዴታዎችና ደንቦች ተፈጻሚነት ለማክበር ነው፡፡

  • ሀ) የሎተሪና ጨዋታ ሕጎችና ደንቦች፣
  • ለ) በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን ለመከላከል፤
  • ሐ) የመረጃ ጥበቃ ሕጎችን ለማክበር፣
  • መ) የግብር ግዴታዎችን ለመወጣት፣

6. መረጃዎን ማጋራትና ይፋ ስለማድረግ

የግል መረጃዎትን ፈቃድዎን ስናገኝ፣ መረጃውን ለማቀናበር ሕጋዊ መሠረት ሲኖር፣ መረጃዎትን ለመጠበቅ አግባብነት ያላቸው የጥበቃ እርምጃዎች መወሰዳቸው ሲረጋገጥና፤ የመረጃ ማጋራቱን ዓላማ እና የተቀባዩን ማንነት እንዲያውቁ በማድረግ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ ብቻ ለሚከተሉት ሦስተኛ ወገኖች ልናጋራ እንችላለን፡፡

  • 6.1 ለአገልግሎት አቅራቢዎች፦ በክፍያ መሠብሠብ፣ በመረጃ ትንተና እና ማንነትን በማጣራትና በማረጋገጥ ስራዎች አገልግሎት ለሚሰጡን አቅራቢዎች።
  • 6.2 ለመንግስት ተቆጣጣሪ አካላት፦ ህጋዊ ግዴታዎቻችንን ለማክበር ወይም ለሚቀርቡ ህጋዊ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት።
  • 6.3 የንግድ ባለቤትነት ዝውውር፡- የንግድ ድርጅቶች ውህደት፣ ግዢ ወይም የንብረት ሽያጭ በሚከሰትበት ጊዜ።

7. የመረጃ ደህንነት

  • 7.1 መረጃዎትን ካልተፈቀደለት ጥቅም፣ ለውጥ እንዲሁም ይፋ መደረግ ለመከላከል በኢንዱስትሪው ደረጃውን የጠበቀ የደህንነት እርምጃዎችን እንተገብራለን።
  • 7.2 የግል መረጃዎትን ያልተፈቀደለት ሰው እንዳይጠቀመውና እንዳያገኘው፣ በአጋጣሚ እንዳይጠፋ፣ ወይም እንዳይበላሽ ለመከላከል ተገቢ የቴክኒክ እና ድርጅታዊ እርምጃዎችን እንተገብራለን፡፡
  • 7.3 መደበኛ የሆነ የመረጃ ደህንነት ግምገማ በየጊዜው እናካሂዳለን።
  • 7.4 የምዝገባ መለያዎትን ደህንነቱን ለመጠበቅ እርስዎም ኃላፊነት አለብዎት፡፡

8. የመረጃ ክምችት

  • 8.1 የእርስዎን ግላዊ መረጃ በዚህ ፖሊሲ ውስጥ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች ለማሟላት፣ በሕግ የተወሰኑ ግዴታዎችን ለመፈጸም፣ አለመግባባቶችን ለመፍታት፣ ወይም ስምምነቶችን ለማስፈጸም ምክንያታዊ ለሆነ ጊዜ ድረስ አከማችተን እናቆያለን።
  • 8.2 ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ግዴታዎችን በማክበር፣ መለያዎትን እና መረጃዎትን ለማስወገድ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

9. የተጠቃሚ መብቶች

ተጠቃሚዎች የሚከተሉትን መብቶች አሏቸው፡-

  • ሀ) የግል መረጃዎን ማየት፣ ማዘመን፣ ወይም ማስተካከል፣
  • ለ) ስለእርስዎ የምንይዘውን መረጃ ቅጂ መጠየቅ፣
  • ሐ) ተቀባይነት ሲኖረው የመረጃዎትን አጠቃቀም በሚመለከት የሰጡትን ፈቃድ ማንሳት፣
  • መ) ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ግዴታዎችን በማክበር፣ መለያዎትን እና መረጃዎትን ለማስወገድ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

10. ኩኪዎች እና የመከታተያ ቴክኖሎጂዎች

  • 10.1 የእርስዎን ተሳትፎ ለማሻሻል፣ አጠቃቀምን ለመተንተን፣ ግለሰባዊ የሆነ ይዘት እና ማስታወቂያዎችን ለማቅረብ ኩኪዎችን እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን።
  • 10.2 የኩኪ ምርጫዎችዎን በድህረገፅ ማሰሻዎ (browser) ላይ የሚገኙ ማስተካከያዎችን በመጠቀም ሊቆጣጠሩ ይችላሉ።

11. ሦስተኛ ወገን አገናኞች

መድረካችን ወደ ሌሎች የሦስተኛ ወገን ድረገጾች የሚወስዱ አገናኞች ሊይዝ ይችላል። ለእነዚህ ድረገጾች የግላዊነት ሥነ ሥርዓቶች ወይም የሚቀርብ ይዘት ተጠያቂነት የለብንም። ለእነዚህ የሦስተኛ ወገን ድህረ ገጾች ማንኛውንም የግል መረጃ ከመስጠትዎ በፊት የግላዊነት ፖሊሲያቸውን ይገምግሙ።

12. የልጆች ግላዊነት

በመድረካችን ለሚቀርብ የሎተሪ እና ፈጣን ጨዋታዎች ተሳታፊነት በሕግ የተገደበ ዕድሜ (18 ዓመት እና ከዚያ በላይ) ካልሆነ መጠቀም አይቻልም፡፡ መድረካችን በማወቅ ዕድሜያቸው ካልደረሱ ልጆች መረጃ አይሰበስብም፡፡

13. ዓለም አቀፍ የመረጃ ሽግግር

ከኢትዮጵያ ውጭ የምትገኙ ከሆነ፣ መረጃዎት በተለያዩ የመረጃ ጥበቃ ሕጎች ያላቸው ሀገራት ሊተላለፍ እና ሊቀናበር ይችላል። መረጃዎትን ለመጠበቅ አግባብነት ያላቸው የጥበቃ እርምጃዎች እንደምንወስድ እናረጋግጣለን።

14. የፖሊሲ ለውጦች

ይህን የግላዊነት ፖሊሲ በየጊዜው ልናሻሽለውና ልናዘምነው እንችላለን። ለውጦችን በድህረ ገጹ ላይ ይታያሉ፣ አገልግሎታችንን መጠቀም በመቀጠልዎ የተሸሻለውን ፖሊሲ እንደተቀበሉ ይቖጠራል፡፡

15. አድራሻ

ስለዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ጥያቄዎች ወይም ቅሬታዎች ካሉዎት፣ በኢሜይል info@ethiolottery.et ወይም በስልክ ቁጥር +251977717272 ያግኙን።